በልደታ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የተመረቁት ስማርት ወረዳ ህንፃዎች በውስጣቸው ምን ምን ይዘዋል?

You are currently viewing በልደታ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የተመረቁት ስማርት ወረዳ ህንፃዎች በውስጣቸው ምን ምን ይዘዋል?

AMN – ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም

“ዛሬ በልደታ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የተመረቁት ስማርት ወረዳ ህንፃዎች “

የልደታ ክፍለከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ሕንፃ

👉12,000 ካ.ሜ አጠቃላይ የወለል ስፋት አለው ፣

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 01

👉 7,260 ካ.ሜ አጠቃላይ የወለል ስፋት አለው

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 12

👉 8,122 ካ.ሜ አጠቃላይ የወለል ስፋት አለው

እነዚህ ዘመናዊ የአስተዳደር ሕንፃዎች እያንዳንዳቸው

👉 ከ60 በላይ ቢሮዎችና ተጨማሪ የስራ ስፍራዎች አሏቸዉ ፣

👉 ስማርት ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸውና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ወገኖች ከግምት ያስገቡ ሊፍቶች አሏቸው፣

👉 የህፃናት ማቆያ ፣

👉 ጂምናዚየም ፣

👉 የመጀመሪያ ሕክምና አገልግሎት መስጫ ፣

👉 400 መቀመጫዎችን መያዝ የሚችሉ መሰብሰቢያ አዳራሾች ፣

👉 ከምድር በታች እና በምድረ ግቢዎቹ የሚገኙ የተሸከርካሪ ማቆሚያዎች ፣

👉 አረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ-ልማቶች የተሟሉላቸው ናቸው፡፡

እነዚህ ዘመናዊ ሕንፃዎች ከዚህ ቀደም እንደምናውቃቸው የወረዳ አስተዳደር ሕንፃዎች አይነት ሳይሆኑ በቀጣይ የሚሰጡ የስማርት (ስሉጥ) ከተማ አገልግሎቶችን ጭምር ታሳቢ ያደረጉ የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማቶችን ያሟሉ ናቸዉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review