በአዲስ አበባ ከተማ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት አማራጭ የገበያ ስፍራዎችን ከማስፍት ባሻገር የቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከር ቁልፍ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

መንግስት የሕዝብን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለመፍታት ባለፉት ጥቂት አመታት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን የገለፁት የውይይቱ ተሳታፊዎች በተለይ በጤናው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች መንግሰት የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር አረጋግጧል ብለዋል፡፡
የኑሮ ውድነት ላይ የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቅለል የገበያ ማእከላትን ብሎም አማራጭ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን የማስፍት ስራ የሚደነቅ መሆኑን ያነሱት የውይይቱ ተሳታፊዎች በቁጥጥር ስራዎች ላይ አሁንም ተጨማሪ ስራን እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰናቀ እንግዳው ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ከነዋሪው ነባራዊ ህይወት ጋር የሚጣጣም ግብይት እንዲኖር የተቀረፁ ፕሮጀክቶች በቅርቡ በይፍ ስራ እንደሚጀምሩም አቶ አስናቀ ተናግረዋል፡፡
ከትራንስፖርት ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች ደግሞ የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ከተማ አስተዳደሩ የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ድጎማ የሚያደር መሆኑን አንስተውሉ የቀረቡትን ችግሮች በማጣራት በቅርቡ ምላሽ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
መድረኩ የሕዝብንና የመንግስትን ጥምረት የሚያጠናክር የሀገርን ልማትም የሚያፋጥን መሆኑም ተገልጿል፡፡
በራሄል አበበ