ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህንድ አቻቸዉ ናሬንድራ ሞዲ እና ከልዑካን ቡድናቸዉ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህንድ አቻቸዉ ናሬንድራ ሞዲ እና ከልዑካን ቡድናቸዉ ጋር ተወያዩ

AMN ታኅሣሥ 7/2018

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነሥርዓት አድርገናል ብለዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ካደረግን በኋላ ከልዑካን ቡድኖቻችን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል።

በውይይታችን በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል እያደገ የመጣውን ትብብር እና የወል ቅድሚያዎች የሚያንፀባርቁ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ቃኘተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል በጉምሩክ የጋራ አስተዳደር ድጋፍ፣ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳታ ማዕከል ምስረታ የመግባቢያ ሥምምነቶችን እንዲሁም በአለምአቀፍ የሰላም ማስከበር ላይ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እና የሚያጠናክረውን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ሥራ የመግባቢያ ሥምምነት የፊርማ ሥነሥርዓት ላይም ተገኝተናል።

ህንድ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ስትሆን የዛሬዎቹ ውይይቶች እና ሥምምነቶችም ለጋራ ጥቅም በተለያዩ ዘርፎች ያሉንን ትብብሮች ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኛ አቋም ያሳያሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review