ኢትዮጵያ በወርልድ ቴኳንዶ አንድ ወርቅ እና አራት የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

You are currently viewing ኢትዮጵያ በወርልድ ቴኳንዶ አንድ ወርቅ እና አራት የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

AMN ታኅሣሥ 9/2018 ዓ.ም.

ዛሬ በአንጎላ ሉዋንዳ በተጀመረው የወርልድ ቴኳንዶ ኢትዮጵያ አንድ ወርቅ እና አራት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

በአንጎላ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ እንደቀጠለ ሲሆን ዛሬ በተጀመረው የወርልድ ቴኳንዶ ላይ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ ድል ቀንቷታል።

በ51 ኪሎ ግራም አብርሃም አዱኛ እልህ አስጨራሽ ፉክክር በማድረግ የወርቅ ሜዳሊያውን ለሀገሩ አስገኝቷል።

አብርሃም አዱኛ ኬንያን፣ አልጀሪያን፣ ሌሴቶን እና ግብጽን በማሸነፍ ነው የወርቅ ሜዳሊያውን ማጥለቅ የቻለው።

በሌሎች ምድቦች በ78 ኪሎ ግራም አብርሃም በቀለ፣ በ52 ኪሎ ግራም ረድኤት መለሰ፣ ሊዲያ ጌታሁን በ59 ኪሎ ግራም እንዲሁም ገነት ብሩክ በ68 ኪሎ ግራም የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

ኢትዮጵያ በውድድር መድረኩ ያገኘችው የወርቅ ብዛትም ሰባት ደርሷል።

በዓለማየሁ ሙሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review