በምድብ 1 ማሊ እና ዛምቢያ ቀን 11:00 ሲል ይገናኛሉ።
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ማሊ በቤልጂየማዊው አሰልጣኝ ቶም ሴንት ፊት የምትመራ ሲሆን በአውሮፓ ሀገራት የሚጫወቱ በርካታ ተጫዋቾችን በስብስቧ አካታለች።
ዛምቢያዎች በአንጻሩ የሌስተር ሲቲውን ፓትሰን ዳካ ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾችን አጣምረው ዛሬ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በምድብ ሁለት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ከአንጎላ ይጫወታሉ።
ከሀገራቸው ክለብ ኦርላንዶ ፓይሬትስ ዘጠኝ ተጫዋቾች በስብስባቸው ያካተቱት ደቡብ አፍሪካዎች ከአውሮፓ እና ሌሎች ሊጎች የመረጧቸውን ተጫዋቾች ይዘው ዛሬ ምሽት 2:00 ከአንጎላ ይጫወታሉ። አንጎላዎች ደግሞ በአውሮፓ እና በአረብ ሀገራት ሊጎች የተውጣጡ ተጫዋቾችን አካተዋል። ምሽት 5:00 ላይ ደግሞ ግብጽ ከዝምባቡዌ ይገናኛሉ።
ግብጾች ለአፍሪካ ዋንጫው አሸናፊነት ቅድመ ግምት ካገኙ ሀገራት የተመደቡ ሲሆን የሊቨርፑሉ አጥቂ እና የብሄራዊ ቡድኑ አምበል መሃመድ ሳላህ ልዩነት ፈጣሪውና ተጠባቂው ተጫዋቾች ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የማንችስተር ሲቲው ኦማር ማርሙሽም ሌላው ፈርኦኖቹ ላይ የቡድን ጥራት የሚጨምር ተጫዋቾች ነው።
የፈርዖኖቹ ዋና አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን ግብፅ በአፍሪካ ዋንጫው የበላይ መሆን እንደሚጠበቅባት ተናግረዋል። ወደ ሞሮኮ የመጣነው ዋንጫ ለማሸነፍ ነው ብለዋል።
ስለ ሞሀመድ ሳላህ ያነሱት አሰልጣኙ “ ሳላህ አሁንም የአለም እግርኳስ ተምሳሌት ነው ፤ ከአለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ሆኖ ይቀጥላል። “ብለዋል።
በዚምባቡዌ በኩል ደግሞ የፕሪሚየር ሊጉ ዎልቭስ ተጫዋች ታዋንዳ ችሬዋ ይጠበቃል።
በዘላለም አቢይ