የዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ግንኙነት ወደ ዲጂታል አማራጮች እየተቀየረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ተሰጥቷል

You are currently viewing የዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ግንኙነት ወደ ዲጂታል አማራጮች እየተቀየረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ተሰጥቷል

‎AMN ታኅሣሥ 13/2018 ዓ.ም

የዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ግንኙነት ወደ ዲጂታል አማራጮች እየተቀየረ በመሆኑ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ገለጹ።

‎የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት ሀሚድ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማጠናቀቂያ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎ዋና ዳይሬክተሯ እንደተናገሩት፣ የዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ግንኙነት ወደ ዲጂታል አማራጮች እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ለነገ የሚባል እና ከዲጂታላይዜሽን ስራዎች ጋር ጎን ለጎን ሊከናወን የሚገባው አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን አሳስበዋል።

‎የፐብሊክ ኪይ መሰረተ ልማት ብለው ካስቀመጡት መካከል የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት፣ ለፋይዳ (ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ) እና ለኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አገልግሎቶች ስኬት መሰረት ይገኙበታል።

በሃገሪቱ ‎የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስጠብቅ (Sovereign Cloud) መሰረተ ልማት ተገንብቶ ለቁልፍ መንግስታዊ ተቋማት አገልግሎት መስጠት መጀመሩም አስረድተዋል።

‎ከዲጂታል ግንኙነት መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶችንና ማጭበርበሮችን ለመከላከል የዲጂታል ፎረንሲክ ምርመራ ስራ መጀመሩን አስታውሰዋል።

‎የሳይበር ጥቃቶች ሲከሰቱ ፈጣን ምላሽ የሚሰጠውን ማዕከል የማስፋፋት ስራ መከናወኑን ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።

‎ወ/ሮ ትግስት አክለውም፣ በማንኛውም የፈጠራ ስራ (Innovation) እና የስታርት አፕ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የደህንነት ጉዳይ እንደ ዋነኛ ምሰሶ ሊታይ እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎በዲጂታል ኢኮኖሚው ላይ አመኔታን (Digital Trust) ለመፍጠር የዜጎችና የተቋማት ደህንነት መጠበቅ ግዴታ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

‎በቀጣይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞ፣ አስተዳደሩ የሀገሪቱን ትላልቅ ተቋማት በንቃት በመጠበቅና ራስን በመቻል ላይ ያተኮሩ የቴክኖሎጂ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review