የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ቀጣይነት ያለው እና ፈጣን ዕድገትን ዕውን ለማድረግ ኢንተርፕረነርሽፕ ቁልፍ መሳሪያ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ቀጣይነት ያለው እና ፈጣን ዕድገትን ዕውን ለማድረግ ኢንተርፕረነርሽፕ ቁልፍ መሳሪያ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – ታኀሣሥ 17/2018 ዓ-ም

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በሁሉም መስክ የሥራ ፈጠራ ባህልን በማስረጽ ቀጣይነት ያለው እና ፈጣን ዕድገትን ዕውን ለማድረግ ኢንተርፕረነርሽፕ ቁልፍ መሳሪያ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ የኢፌዲሪ ኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ረቂቅ ፖሊሲን በተመለከተ ከዲጂታል ካውንስል አባላት ጋር በበይነ መረብ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።

የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ፖሊሲ በዋናነት ሁሉን አቀፍ እና አካታች ሀገራዊ የኢንተርፕረነርሽፕ ንቅናቄን በማቀጣጠል በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ጋር ተጣጣሚ በሆነ መልኩ የዲጂታል ሥራ ፈጠራንና ተወዳዳሪነትን የሚያበረታታና የሚደግፍ ነው።

የፖሊሲ ማዕቀፉ ችግር ፈች ማህበረሰብን ለመገንባት፣ የፈጠራ ባህልን ለመጎልበት፣ እሴትን ለመጨመር እንዲሁም ምቹ ስነምህዳርን ለመገንባት የሚያስችል የኢኮኖሚ ዕድገት ማዕቀፍ ነው ሲሉም አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሀገራችንን የኢንተርፕረነርሽፕ ስነ-ምህዳርና የስራ ፈጠራ ውጥኖችን አቅጣጫ በመስጠት የመምራት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት።

በተለይ የኢንተርፕረነርሽፕ ስነ-ምህዳሩን ሊያሻሽሉ የሚችሉ የጋራ አመለካከቶችን፣ እምነቶችንንና ባህሪያትን ለማጎልበት በዕጅጉ ያግዛል።

ይህ የልማት ፖሊሲ የታለመለትን ውጤት ማምጣት እንዲችል በፖሊሲው ትግበራ ወቅት የሚታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በመለየት በየደረጃው ወጥና ጠንካራ የክትትል ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ከዲጂታል ካውንስሉ ጋር መግባባት ፈጥረናል ብለዋል።

በመጨረሻም በኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ እና ግብዓቶችን በመጨመር የልማት ፖሊሲ ሰነዱ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተልኮ እንዲፀድቅ ወስነናል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review