መገናኛ ብዙሀን የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት ከማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ተገለጸ

You are currently viewing መገናኛ ብዙሀን የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት ከማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ተገለጸ
  • Post category:ቱሪዝም

AMN ታኅሣሥ 21/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን የመዲናዋን የቱሪዝም ሀብቶች ለማስተዋወቅና ተደራሽ ለማድረግ ሊያግዝ በሚያስችል መልኩ የከተማ ቱሪዝም ጽንሰ ሐሳብና አዘጋገብ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የስልጠናና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።

የኮሚሽኑ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን አይናቸው ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት እንዲሁም ቀጣይ እቅዶችን በማስመልከት ለተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል።

በቱሪዝም ዘርፉ በጋዜጠኝነት እያገለገሉ የሚገኙት ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ በበኩላቸው፤ የከተማ ቱሪዝም አዘጋገብ እና ስነምግባር ዙሪያ ምልከታቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ፤ ቱሪዝም እና መገናኛ ብዙሀን የማይነጣጠሉ መሆኑን ገልጸው በተለይ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት በማስተዋወቅ ቁልፍ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል።

በቱሪዝም ዘርፍ ላይ የሚሰሩ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሙሉ እውቀት እና መረጃ በማግኘት የመዲናዋን የቱሪዝም ሀብቶች ተደራሽ የማድረግ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሚሽኑ ከሁሉም የመገናኛ ብዙሀን ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑንም መግለጻቸዉን ኮሚሽኑ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review