በየዘርፎች እያሳካን ያለነው ስኬት የኢትዮጵያን መቻል ያሳየ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ

You are currently viewing በየዘርፎች እያሳካን ያለነው ስኬት የኢትዮጵያን መቻል ያሳየ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ

AMN ጥር 4/2018 ዓ.ም

በየዘርፎች እያሳካን ያለነው ስኬት የኢትዮጵያን መቻል ያሳየ ነው ሲሉ በሚንስትር ማዕረግ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ተናገሩ።

የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በ6 ወር ውስጥ እንደ ሀገር የተከናወኑ ስራዎችና የተገኙ ስኬቶችን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ፤ መንግስት ለሚያድግ ህዝብ ፍላጎት የሚያድግ የኢኮኖሚ መንገድ እየተከተለ ይገኛል ብለዋል።

የአለምን የአየር ትራንስፓርት የሚወዳደርና ቀዳሚ መሆን የሚያስችል የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ኢትዮጵያን የአፍሪካና የአለም የአየር ትራንስፓርት በር ያደርጋታል ሲሉ ገልፀዋል።

የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠርና አላስፈላጊ ህገ ወጥ የግብይት ሰንሰለትን በመበጣጠስ፣ የቅዳሜና የእሁድ ገበያን በማስፋፋትና ድጎማ በማድረግ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ስለመቻሉ አንስተዋል።

ባለፉት 6 ወራት በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረግ ሂደት በተለያዮ የሀገሪቱ ክልሎች በመስኖና በኩታ ገጠም እርሻዎች ሰፊ መሬትን በሰብል በመሸፈን ምርታማነትን ማሳደግ ስለመቻሉ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ገልፀዋል።

ከከተማ ባሻገር ሞዴል የገጠር መንደሮች ዜጎች ታሪካቸውን የሚመጥን ኑሮ እንዲኖሩ በማስቻል አርሶ አደሩ ንፁህ በሆነ የመኖሪያ ከባቢ ልጆቻቸውን እንደመያሳድጉ ስለመደረጉ ጠቅሰዋል።

በኢንዱስትሪ ዘርፍ በተሰራ ስራ በመፍጠር፣ መፍጠንና መዝለል መርህ የማምረቻ ቦታዎችን በማመቻቸት ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት ተችሏል ብለዋል ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ።

ለአመትት ተዘንግተው ቆይተው የነበሩትን የማዕድንና የቱሪዝም ዘርፎች በማነቃቃት የኢትዮጵያን የተፈጥሮ እምቅ ሀብት በመጠቀም ኢትዮጵያ ከእነዚህ መስኮች ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ መደረጉን ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ በመግለጫው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዲጅታል መስክ ያሳካችውን የ2025 የዲጅታል ኢትዮጵያ ጉዞ በዲጅታል ኢትዮጵያ 2030ም በተለያዮ ዘርፎች ለመድገም በስፋት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ያለፈው 6 ወር በዲፕሎማሲ ዘርፍ ኢትዮጵያ በሰራችው ተግባር የተለያዮ ሀገራት መሪዎች ኢትዮጵያን ከመጎብኘታቸው ባሻገር በተለያዮ ዓለም አቀፍ መድረኮች በመሳተፍ ከሀገር አልፎ ለአፍሪካ ኩራት መሆን የተቻለበት እንደነበር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ተናግረዋል።

የህዝብን ጥያቄዎች በተገቢው ሁኔታ በሀላፊነት ለመመለስ ያስችል ዘንድ የፊት ለፊት ውይይቶችን በማዘጋጀት ስለመሰራቱ ጠቅሰዋል።

በቀጣይ የሚካሄደደውን ሀገራዊ ምርጫና ሀገራዊ ምክክር ፍትሀዊ፣ አካታችና የተሳካለት ለማድረግ የተለያዮ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው በመግለጫው ተመላክቷል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review