7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡
ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በምክክር መድረኩ ፣ የ7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እና የምክር ቤቶች ሚና ፣ የሕግ ኦዲት እና የፐብሊክ በጀትና ፋይናንስ ትንተና ጥናት ሰነዶች ላይ ምክክር እንደሚደረግባቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ገልጸዋል።
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ፣ ሠላማዊና ፍትኅዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ነው አፈ-ጉባኤው ማብራራታቸዉን ምክር ቤቱ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡