በወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት አቧራውን አራግፈን የደበዘዘዉን ታሪካችንን እና ቅርሶቻችንን በተጨባጭ አልምተናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing በወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት አቧራውን አራግፈን የደበዘዘዉን ታሪካችንን እና ቅርሶቻችንን በተጨባጭ አልምተናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ
default

AMN ጥር 7/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነዉ የወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክት አቧራውን አራግፈን የደበዘዘዉን ታሪካችንን እና ቅርሶቻችንን በተጨባጭ አልምተናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ለዓመታት ትኩረት ተነፍጎት የቆየውን የኮርያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክን የጎበኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ላይ ለጀግኖች የሚመጥን ክብር ተላብሶ ለከተማዋ ተጨማሪና አዲስ ውበት ተላብሶ መልማቱን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ ለጀግኖች በሚመጥን መልኩ ክብር ተጎናጽፏል ነዉ ያሉት፡፡

ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ እየተከናወኑ የወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋዉረዉ በመጎብኘት በሰጡት ገለጻ ፓርኩ ለረጅም ዓመታት ትኩረት ተነፍጎት መቆየቱን አንስተዋል፡፡

default

አካባቢዉ የወንጀለኞች መሸሸጊያና የአልባሌ ተግባራት መከወኛ ሆኖ ቆይቷል፡፡

“አሁን ላይ ግን አቧራውን አራግፈን የደበዘዘዉን ታሪካችንን እና ቅርሶቻችንን በተጨባጭ አልምተናል” ሲሉ ለፓርኩና ለሙዝየሙ የተሰጠውን አዲስ ህይወት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብራርተዋል።

በአካባቢዉ ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ ጅምናዝየሞች ፣ የካፌቴሪያ እና ውብ የእግረኛ መንገዶች ተገንብተውበታል፤ የፈራረሱና መንገድ አልባ የነበሩ መገዶች ተስተካክለዋል፤ የወንጀለኞች መደበቂያ የነበሩ ስርቻዎች ጠርተዉ አካባቢው ብርሃንና ውበት እንዲላበስ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የኮርያ ዘማቾች ሙዝየም ብዙም ያልተነገረለት ታሪካዊ ስፍራ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ላይ የጀግኖች ታሪክ እና ቅርስ ለምቶ ትውልድ እንዲዘክራቸው መደረጉንም ገጸዋል፡፡

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review