የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈጥሮን እና የትናንትን ወረት ለነጋችን ብሩኅነት በአንድ እንደሚያሰባስብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተለለፉት መልዕክት ዛሬ ጠዋት በመረቅነው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ይኽን በግልጽ ተመልክተናል ብለዋል። ሥራው ከአካባቢው በተገኙ የግንባታ ቁሳቁሶች እና በአካባቢ አቅም የተገነባ በመሆኑ ዘላቂነትን እና ባለቤትነትን ያንፀባርቃል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በባሕል፣ በተፈጥሮ እና ታሪካዊ ጥሪቶች የታደለች በመሆኗ ዛሬ ያለንን ጉልበት እና ጥንካሬ ለመጪዎቹ ተከታታይ ትውልዶች በሚተርፍ መንገድ ሀብቶቿን መግለጥ መቀጠል ይኖርብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።