ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በታሪካዊው የፋሲለደስ ባሕረ ጥምቀት ማክበራቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በታሪካዊው የፋሲለደስ ባሕረ ጥምቀት ማክበራቸዉን ገለጹ

AMN ጥር 11/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የመገለጥ እና የዕርቅ በዓል ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

ጥምቀት በጎንደር ልዩ ነው። ድምቀቱ፣ ታሪካዊነቱ፣ ድባቡ ሁሉ ድንቅ ነው። ከሀገሬው እስከ ውጭ ሀገር ዜጎች እልፍ ሕዝብ የታደመበትን የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በታሪካዊው የፋሲለደስ ባሕረ ጥምቀት ተገኝተን አክብረናል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በድጋሜ እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review