በአዲስ አበባ የተገነቡ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የቀየሩ ናቸው – ሚስተር ጄምስ ኒጆሮጂ የናይሮቢ ከተማ ምክትል ገዥ

You are currently viewing በአዲስ አበባ የተገነቡ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የቀየሩ ናቸው – ሚስተር ጄምስ ኒጆሮጂ የናይሮቢ ከተማ ምክትል ገዥ

AMN- ጥር 17/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ ላይ በየዕለቱ አዳዲስ ፕሮጀክቶች እየተጠናቀቁ ለተጠቃሚ ክፍት መሆናቸው አሁን ላይ ዜና ከመሆን አልፎ ባሕል እየሆነ መጥቷል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

በከተማዋ እየታዬ ያለው ለውጥ ለራሳችን አግራሞት ፈጥረው እጅን በአፍ ከማስጫን ባለፈ በደራሽ እንግዶችና የሌሎች ሀገራት ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን ጭምር ውበቷን በአንድ ቃል አስደማሚ እያሉ መግለጽ ከጀመሩ ውለው አድረዋል።

ከወደ ሰሞኑ አዲስ አበባን ለመጎብኘት ዕድል ካገኙ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች መካከል የናይሮቢ ከተማ ምክትል ገዥ ሚስተር ጄምስ ኒጆሮጂ አንዱ ናቸው።

ሚስተር ጄምስ የአዲስ አበባ ከተማን የወንዝ ዳርቻ ልማትና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸው በሰጡት ምስክርነት የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት በጣም አስደማሚና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ከተሞች አርአያ እና ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ የተሠራው የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ በጣም መሳጭ ነው፣ ናይሮቢን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ጭምር ለማስፋት ጥሩ ምሳሌ የሚሆን ሥራ በአዲስ አበባ ተመልክተናል፣ ለዚህም ለከተማ አስተዳደሩና ለሀገሪቱ አመራሮች ምስጋና ይገባቸዋል በማለት ገልጸዋል ።

በናይሮቢ ከተማ ያሉ ወንዞች የተበከሉና ለዕይታ የማይማርኩ ናቸው፤ በመሆኑም ከአዲስ አበባ ተሞክሮ በመነሳት ወንዞቹን የማልማት ሥራ ለመስራት ትምህርት እንዳገኙ ነው ምክትል ገዥው የገለፁት ።

በአዲስ አበባ የተገነቡ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የቀየረና ከከተማዋ ነዋሪ በተሰበሰበ ግብር የተሠራ መሆኑ ደግሞ በጣም የሚያስደስት መሆኑን ነው ሚስተር ጄምስ ኒጆሮጂ የገለጹት።

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review