የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋጋና ጤናማ የፋይናንስ ስርአት እንዲኖር አስችሏል – አቶ አህመድ ሽዴ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋጋና ጤናማ የፋይናንስ ስርአት እንዲኖር አስችሏል – አቶ አህመድ ሽዴ
  • Post category:ኢኮኖሚ

AMN – ጥር 19/2018 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ45 ሚሊዬን በላይ የሚሆኑ ደንበኞቹን ለማመስገን ያለመ የደንበኞች አገልግሎት ሳምንት የመክፈቻ መርሀ ግብር አካሂዷል ።

ባንኩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚያከብረው የደንበኞች አገልግሎት ሳምንት “የደንበኞች እርካታ የባንካችን ስኬት ነው” በሚል መሪ ቃል ነው ።

የኢፌድሪ የገንዘብ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብስቤ አቶ አህመድ ሽዴ ኢትዮጵያ ባለፋት ጥቂት አመታት ባከናወነችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ባለፈው በጀት አመት ብቻ ዕድገቷን ወደ 9.2 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ በፋይናንስ ዘርፍ በርካታ ተግባራት ስለመከናወናቸው የገለፁት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋጋና ጤናማ የፋይናንስ ስርአት እንዲኖር የጀርባ አጥንት ሆኗል ብለዋል።

ባንኩ ትልቁ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተዋናይ ከመሆኑ አንፃር ከፍተኛ አበርክቶ እንደሚጠበቅበት የተገለፁት አቶ አህመድ ሽዴ በሀብት አሰባሰብ፣ በፋይናንስ አካታችነት እና በዲጂታላይዜሽን የሚጫወተውን የመሪነት ሚና በማላቅ የደንበኞች እርካታን ከፍ ለማድረግ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኦፕሬሽን ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ፍቅረስላሴ ዘውዱ ባንኩ የደንበኞችን እርካታ ከፍ ለማድረግ አገልግሎቱን ከማዘመን እና ተደራሽነትን ከማስፋት ጀምሮ በርካታ ስራዎች ስለመስራቱ አንስተዋል።

በመርሃ ግብሩ ባንኩ ለደንበኞቹ አክብሮቱን የሚገልፅበት ደንበኛ ተኮር አገልግሎትን የሚሰጥበትና የሚያመሰግንበት ስለመሆኑም ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለዋል ።

ባንኩ የደንበኞችን እርካታ ከፍ ለማድረግ የደንበኞች ተሞክሮ ስትራቴጂን በመቅረፅ ክትትል በማድረግ ቴክኖሎጂን በማስፋትና የተቋሙ ሰራተኞችኝ የደንበኛ አያያዝ ክህሎት ስልጠና በመስጠት የተገልጋዩ እርካታ የባንኩ ስኬት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አቶ ፍቅረስላሴ ዘውዱ ተናግረዋል ።

በራሔል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review