AMN- ጥር 20/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና የዩኤስ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በጽሕፈት ቤታችን ከተገኙት የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና የዩኤስ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
ቀጣይነት ያለው ትብብር እና መከባበርን አፅንዖት ለሰጠው ደማቅ እና ገንቢ ውይይታችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ በማለትም አክለዋል::