በአራዳ ፓርክ የኮሪደር መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሰዉ አሽከርካሪ 100 ሺህ ብር ተቀጣ

You are currently viewing በአራዳ ፓርክ የኮሪደር መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሰዉ አሽከርካሪ 100 ሺህ ብር ተቀጣ

AMN ጥር 20/2018

በአራዳ ፓርክ በብስክሌት መንገድና በመሮጫ ትራክ ላይ መኪና በማሽከርከር በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሰዉ አሽከርካሪ 100 ሺህ ብር ተቀጥቷል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ራስመኮንን አካባቢ ጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት አካባቢ አራዳ ፓርክ ውስጥ በብስክሌት መንገድና በመሮጫ ትራክ ላይ መኪና በማሽከርከር መሰረተ-ልማቱን ያበላሸውን አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር በማዋል 100ሺህ ብር መቅጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡

ባለስልጣኑ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት አሽከርካሪውን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን ገልጿል።

ጥቆማ ለሚሰጠው ህብረተሰቡ ምስጋና ያቀረበዉ ባለስልጣኑ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማት፣ በወንዞች ዳርቻና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን ጉዳት በሚያደርሱት እና ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ በመቀጠል ሀላፊነቱ እንዲወጣ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review