ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ለ3.4 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ለ3.4 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ጥር 26/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፤ በሀገሪቱ እየተተገበረ ባለው አዲስ የአሰራር ሥርዓት በመታገዝ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንዖት ሰጥተው እንደተናገሩት፣ ይህ ስኬት ቀደም ሲል በአንድ ዓመት ውስጥ ይሳካ የነበረውን ግብ በግማሽ ዓመት ውስጥ ማሳካት የተቻለበት ልዩ አጋጣሚ ነው።

በአዲሱ የተቀናጀ አሰራር አማካኝነት የታዩ ውጤቶች አስገራሚ መሆናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 2.6 ሚሊዮን ዜጎች ስራ ያገኙ ሲሆን፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የታከሉትን ጨምሮ ቁጥሩ ወደ 3.3 – 3.4 ሚሊዮን ከፍ ብሏል ብለዋል።

ከ350 ሺህ በላይ ዜጎች በውጭ ሀገራት የስራ ዕድል አግኝተዋል። ከእነዚህም መካከል ከ7 እስከ 10 ሺህ የሚሆኑት በጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ሳውዲ አረቢያ የሚሰሩ ባለሙያ (Skilled Professionals) ናቸው።

በአዲስ መልክ የተጀመረውና ዜጎች እዚህ ሀገር ውስጥ ሆነው ለውጭ ኩባንያዎች በኢንተርኔት የሚሰሩበት ዘርፍ ሲሆን፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ 20 ሺህ ወጣቶች ተጠቃሚ ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ውጤት መገኘት በምክንያትነት የጠቀሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካካል የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማቶች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አዳዲስ የነፃ ንግድ ቀጠናዎች (Free Trade Zones) ሰፊ የስራ ዕድል ፈጥረዋል።

በግብርና፣ በማዕድን እና በግንባታ ዘርፎች ላይ የተደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴ እና ህጋዊ የውጭ ስራ ስምሪት፤ ዜጎች ሰልጥነው፣ ቋንቋ አውቀውና በባንክ ሂሳብ ታግዘው በክብረት እንዲሰሩ የሚያስችል ጤናማ ሥርዓት መዘርጋቱ መሆኑን ጠቁመዋል።

ውጤቱ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም አሁንም ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፤ ምክንያቱም የሰው ኃይላችን ቁጥር ከፍተኛ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

መንግስት በቀጣይነት የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የነዳጅ ማጣሪያ (Refinery)፣ የኤርፖርት ግንባታ እና የክሪፕቶ ማይኒንግ ስራዎች ሲጠናከሩ ይበልጥ ሰፊ የስራ ዕድል እንደሚፈጠር አመላክተዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review