AMN- ጥር 27/2ዐ18 ዓ.ም
7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ተዓማኒ፣ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ፡፡
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲያደርግ የነበረዉን ውይይት አጠናቋል፡፡
ቦርዱ በሁለት ቀናት ቆይታዉ ከሀገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፤ ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ከከተማ መስተዳድር ከንቲባዎች፣ ከፌደራልና ከክልል የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልእክት በምርጫዉ ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም በምርጫ ኦፕሬሽንና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ተከታታይ ስብሰባዎች እንደሚኖሩ አስታውሰዋል።
7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ተዓማኒ፣ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊነቱ የሚረጋገጠዉ የምርጫ ቦርድ በሚያደርገው ጥረት ብቻ ባለመሆኑ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የድርሻቸዉን እንዲወጡ መጠየቃቸዉን የቦርዱ መረጃ ያመለክታል።