የአዲስ አበባን ሰላም በማስጠበቁ ሂደት የወጣቱ ሚና ጉልህ ነው

You are currently viewing የአዲስ አበባን ሰላም በማስጠበቁ ሂደት የወጣቱ ሚና ጉልህ ነው

AMN- የካቲት 3/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባን ሰላም በማስጠበቁ ሂደት የወጣቱ ሚና ጉልህ መሆኑን የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን “ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የወጣቶች ውይይት ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ-ግብሩ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ የወጣቱ ሚና ጉልህ መሆኑን ገልጸዋል።

“ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና፣ የሰለጠነ ወጣት በመፍጠር ሂደት ውስጥ ወጣቱ ግንዛቤ የጨበጠበት እንደሆነም ኃላፊዋ ተናግረዋል።

መድረኩ የ2018 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ ፍትሃዊ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቱ ጥሩ ግንዛቤ ያገኘበት መሆኑንም ገልጸዋል።

የሰለጠነ ወጣት በምክንያት የሚያምን መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊዋ፣ ወጣቱ በሀገር የብልጽግና ጉዞ ውስጥ እራሱን አካቶ የሚራመድ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የጠላቶችን ሴራ የተረዳ ወጣት መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊዋ፣ ወጣቱ በሀሰተኛ መረጃዎች ባለመወሰድ ሀገርን የሚከላከል ፊትአውራሪ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review