AMN የካቲት 03 ቀን 2018 ዓ.ም
በማይክል ካሪክ እየተመራ ጥሩ ጉዞ ላይ የነበረው ማንችስተር ዩናይትድ ከዌስትሃም ጋር 1ለ1 በመለያየት ነጥብ ጥሏል።
በጨዋታው ዌስትሃም ቶማስ ሱቼክ ባስቆጠረው ግብ ቢመራም ውጤቱን አላስጠበቀም።
ዩናይትድ ተቀይሮ የገባው ቤንጃሚን ሼሽኮ 96ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ግብ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
ማንችስተር ዩናይትድ በማይክል ካሪክ እየተመራ ያለመሸነፍ ጉዞውን አስቀጥሏል። በጥሩ ብቃት አራት ተከታታይ ድል ያስመዘገበው ዩናይትድ በዛሬው ጨዋታ ግን በዌስትሃም ተፈትኗል።
ውጤቱን ተከትሎ ዩናይትድ 45 ነጥብ በመያዝ 4ኛ ደረጃውን አስጠብቋል። ዌስትሃም በአንፃሩ በ24 ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሸዋንግዛው ግርማ