AMN- የካቲት 13/2018 ዓ.ም
በፈረንሳይ ሌቪን በተከናወነ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር በሴቶች 3000 ሜትር የተሳተፈችው ፍሬወይኒ ኃይሉ በቀዳሚነት አጠናቃለች፡፡
ፍሬወይኒ ርቀቱን ለመጨረስ የወሰደባት 8:24.59 ሰዓት የዓመቱ ፈጣን ተብሎላታል፡፡ በርቀቱ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አለሽኝ ባወቀ 2፡26.29 በመግባት 2ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች፡፡
በተመሳሳይ 3000 ሜትር ወንዶች አዲሱ ይሁኔ አሸንፏል፡፡ አትሌቱ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 7:33.58 ሰዓት ፈጅቶበታል፡፡ በዚሁ ርቀት የተሳተፈው ጌትነት ዋለ 3ኛ ወጥቷል፡፡
በሴቶች 800 ሜትር የማሸነፍ ቅድመ ግምት አግኝታ የነበረችው ፅጌ ዱጉማ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ ውድድሩን እንግሊዛዊቷ ኪሊ ሄጅኪንሰን አሸናፊ ሆናለች፡፡ አትሌቷ የገባችበት 1:54.87 ሰዓት በቤት ውስጥ ውድድር የርቀቱ አዲስ የዓለም ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በሴቶች 1500 ሜትር ብርቄ ሀየሎም 2ኛ እንዲሁም ሳሮን 3ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ