በኢትዮጵያ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ለኢንዱስትሪው ዕድገት መሠረት ጥለዋል — ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ለኢንዱስትሪው ዕድገት መሠረት ጥለዋል — ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN — የካቲት 13/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ማነቆዎች ለመፍታት ትልቅ መሠረት መጣላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የ”አዲስ አበባ ታምርት” ንቅናቄን አስመልክተው ከንቲባዋ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት ኢንዱስትራላይዜሽን ለኢትዮጵያ የማይቀርላት መዳረሻ መሆኑን በመረዳት ግልጽ ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን በዘርፉ ላይ የሚታዩ ዋና ዋና ማነቆዎችን የመለየት ሥራ ተከናውኗል።

በተለይም ኢንዱስትሪውን ሲፈትኑ የቆዩትን የመሠረተ ልማት፣ የፋይናንስ፣ የምርታማነት እንዲሁም የጥራት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

መንግሥት የፈጠረው ምቹ የፖሊሲ ማዕቀፍ እና የፋይናንስ ድጋፍ፣ ባለሀብቶች ከንግድ ዘርፍ ተረካቢነት ተላቀው ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት እንዲሸጋገሩ ትልቅ ዕድል መፍጠሩንም ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review