የአዲስ አበባ ውበት በዓለም ዙሪያ በርካቶችን እያነጋገረ ነው

You are currently viewing የአዲስ አበባ ውበት በዓለም ዙሪያ በርካቶችን እያነጋገረ ነው

AMN – የካቲት 13/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ውብ መልኮች በማህበራዊ ትስስር መድረኮች በስፋት እየተዘዋወሩ አድናቆት እየጎረፈ ነው፡፡

ከቀናት በፊት የቱርክ ፕሬዘዳንት ረጀብ ጣይፕ ኤርዶዋን አቀባበል ሲደረግላቸው የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል መለቀቁን ተከትሎ ነው የማሕበራዊ ሚዲያ የአድናቆት ማዕበሉ የተቀሰቀሰው፡፡

ኢንተርናሽናል ኦብዘርቨር የተባለ የኤክስ(ትዊተር) ገጽ የአዲስ አበባን መሰረተ ልማት በማድነቅ ፣ ከአንዳንድ የመጀመሪያ ደረጃ ከሚባሉ ሀገራት የተሸለ እንደሆነ አግራሞቱን ገልጿል፡፡

ሩሲያ ኒውስ አስደናቂው የአቀባበል ቪዲዮ በሚል ጽሑፍ ተንቀሳቃሽ ምስሉን አጋርቷል፡፡

ሳውዝ ኢስያ ኢንዴክስ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ሚዲያ በአሉታዊ መሳሏን ገልጾ፣ ሆኖ ግን በአዲስ አበባ የኤርዶዋንን አቀባበል ቪዲዮ ሰዎች እየተቀባበሉት መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ቻክሃም የተሰኘ ገጽ “አዲስ ሞዴል” አዲሱ ከተማ ወርቃማ መመዘኛ ሆኗል ሲል አድንቋል፡፡

ከኬንያ እስከ ህንድና ፓኪስታን ከተሞቻቸውን በመመልከት ለምን እንደ አዲስ አበባ አንመስልም በማለት እየጠየቁ መሆናቸውንም ጠቅሷል፡፡

ሻማ ጁኔጆ የተባለ የኤክስ(ትዊተር) ገጽ አዲስ አበባ የአፍሪካ ዳይመንድ መሆን አለባት ሲል ገልጿል፡፡

አፍሪካ ፈርስት የተሰኘ ገጽ በበኩሉ አዲስ አበባን ከሚያሳይ ቪዲዮ ጋር ይህ አሜሪካ ኒውዮርክ ወይም ቤጂንግ ቻይና አይደለም፤ ይህ ረጂብ ጣይፕ ኤርዶዋን የያዘው አጀብ የሚታየው አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ሲል በአድናቆት አጋርቷል፡፡

የኤርዶዋን አቀባበልን የሚያሳየው ቪዲዮው 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ5 ሚሊየን በላይ እይታ ማግኘቱ ነው የተገለጸው፡፡

ውበቷ የተገለጠው የአዲስ አበባ መልክ አፍሪካ በዓለም ሚዲያዎች የተሳለችበትን ትርክት በመቀየር እረገድ አወንታዊ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review