የኮሪደር ልማት የመንግስት እሳቤዎችን ግዝፈት፣ የልማት አካታችነትንና የስራ ጥራትን በግልጽ ያሳየ መሆኑን ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ

You are currently viewing የኮሪደር ልማት የመንግስት እሳቤዎችን ግዝፈት፣ የልማት አካታችነትንና የስራ ጥራትን በግልጽ ያሳየ መሆኑን ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ
  • Post category:ኮሪደር

AMN- የካቲት 16/2018 ዓ.ም

የኮሪደር ልማት የመንግስት እሳቤዎችን ግዝፈት፣ የልማት አካታችነትንና የስራ ጥራትን በግልጽ ያሳየ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ከክልልና ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች እና ተጠሪ ተቋማት ጋር እየገመገመ ነው።

በዚሁ የግምገማ መድረክ የተገኙት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ በከተሞች እየተስፋፋ የመጣው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስችሏል።

በልማቱ የመንግስታችን እሳቤዎች፣ የልማታችችንን አካታችነት የህልማችን ግዝፈት የሥራችንን ጥራት ማሳየት ችለናልም ብለዋል።

ይህንን ተግባር ወደ ገጠር ኮሪደር በማስፋፋት የሀገርን ብልጽግና እያረጋገጥን ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ ልማቱ ለዘርፉ በርካታ እድሎችን ይዞ መጥቷል ሲሉ አክለዋል።

የተጀመረውን የልማት ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል የባለድርሻ አካላት የህዝብና የመንግስት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑንም ሚኒስትሯ አንስተዋል።

እያደገ የመጣውን የከተሜነት ፍላጎትና ፍልሰት በአግባቡ ለመምራት መንግስት ለከተሞች እድገትና መስፋፋት፣ ለዜጎች ኑሮ መቃናት በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

በከተሞች የቤት ልማት አማራጮች እንዲሰፉም የግል አልሚዎች በስፋት እንዲሳተፉ እንዲሁም በማህበራት፣ በመንግስትና በባለሀብቶች ጥምረት ለመስራት አቅጣጫ መቀመጡንም ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱም የታለመውን ሥራ ለማከናወን የሚያስችል አዲስ የቤት ልማት ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ሥራ መገባቱን አንስተዋል።

ይሄው ፖሊሲ የነዋሪዎችን ፍላጎትና ጥያቄ እንዲመልስ የሁሉንም ርብርብና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review