የአዲስ አበባን የኮሪደር ልማት እና የወንዝ ዳርቻ ስራዎችን የሚያስተዋውቅ የፎቶ አውደ ርዕይ ተከፈተ

You are currently viewing የአዲስ አበባን የኮሪደር ልማት እና የወንዝ ዳርቻ ስራዎችን የሚያስተዋውቅ የፎቶ አውደ ርዕይ ተከፈተ

AMN – ሰኔ 26/2018 ዓ.ም

3ኛው የቴክኖ ኢትዮጵያ የፎቶ አውደ ርዕይ በህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ኮምፕሌክስ ለሚቀጥሉት አስር ቀናት የሚቆይበትን መርሃ-ግብር ይዞ ተጀምሯል።

የፎቶ አውደ ርዕዩ የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን ከቴክኖ ኢትዮጵያ፣ ከቦርድ ሴል ፎን አዲስ አበባ እና የአዲስ አበባ ቲያትር ቤቶች አስተዳደር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

በቴክኖ ኢትዮጵያ አዲሱ ካሞን 50 ፕሮ ስልክ የተነሱ፣ የተለያዩ የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የተፈጥሮ ገፀ በረከቶች፣ ታሪኮችና የተለያዩ እይታዎችን የሚያንፀባርቁ አንድ መቶ ፎቶግራፎች በአውደ ርዕዩ ለዕይታ በቅተዋል።

ኮሚሽኑ፣ ቴክኖ ኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ቲያትር ቤቶች አስተዳደር በቱሪዝም እና በቴክኖሎጂ መስክ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ይህ አጋርነት የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ፣ ብሎም የዜጎችን ሀገር የመጎብኘት ልምድ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።

በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

ለአስር ቀናት ቆይታ የሚኖረውን ይህንን ኤግዚቢሽን ከዓስር ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review