ሪያል ማድሪድ እና ፓሪሰን ዠርማ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

You are currently viewing ሪያል ማድሪድ እና ፓሪሰን ዠርማ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

AMN- የካቲት 19/2018 ዓ.ም

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ እና ፓሪሰን ዠርማ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።

በሜዳው ሳንቲያጎ ቤርናቢዩ ቤኔፊካን ያስተናገደው ሪያል ማድሪድ 2ለ1 አሸንፏል።

ኦሬሊዮ ቹአሜኒ እና ቪኒሺየስ ጁኒዮር የስፔኑን ክለብ የማሸነፊያ ግቦች በስማቸው አስመዝግበዋል። ራፋ ሲልቫ የቤኔፊካን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።

በውዝግብ የታጀበውን የመጀመሪያ ጨዋታ 1ለ0 ያሸነፈው ማድሪድ በድምር ውጤት 3ለ1 በመርታት ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።

ማድሪድ 16 ክለቦች በሚሳተፉበት ጥሎ ማለፍ ማንችስተር ሲቲን አልያም ስፖርቲንግ ሊዝበንን ይገጥማል።

የባለፈው ዓመት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊአሸናፊው ፓሪሰን ዠርማ በፓርከ ደ ፕሪንስ ሞናኮን ገጥሞ 2ለ2 ተለያይቷል።

የመጀመሪያውን ጨዋታ 3ለ2 ያሸነፈው የፓሪሱ ክለብ በድምር ውጤት 5ለ4 በማሸነፍ ጉዞውን አስቀጥሏል።

የሊውስ ኤነሪኬው ቡድን በቀጣዩ ዙር ባርሴሎና ወይም ቼልሲን ያገኛል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review