************************
የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማሕተም፥ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነየዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማሕተም፥ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነ#addismedianetworkት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡
ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለነጻነት ለሉዓላዊነት በከፈሉት መስዋዕትነት ዛሬም ድረስ ትውልድ እያመሰገናቸው ይኖራል፡፡
ከ12ቱ የጦር መሪዎች መካከል የዓድዋ ጀግና፥ የዛግዌ ስርወ መንግሥት ተወላጆች ከሆኑት የላስታ መሪዎች አንዱ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ በጀግና ስማቸው አባ መርከብ ይገኙበታል፡፡
የጣሊያኖች ግንባር ቀደም ምንጮች እንደጠቆሙት የዋግሹም ጓንጉል ሠራዊት ጠብመንጃ የያዘና በሚገባ የታጠቀ ሲሆን ብዛቱም ከ10 ሺህ እስከ 11 ሺህ ይደርስ ነበር፡፡
ሠራዊታቸው ታኅሣሥ 7 ቀን 1887 ዓ.ም ከራስ መንገሻ ዮሐንስ ጦር ጎን በማሰለፍ በአምባላጌ ተራራ የጦር ውጊያ ላይ ታላቅ ጀብዱ ሠርተዋል፡፡
በዓድዋ ጦርነት የዋግሹም ጓንጉል ብሩ ሠራዊት ከ4 መቶ በላይ የጣሊያን ወታደሮችና ባለ ማዕረግ የጦር መሪዎችን /መኮንኖችን/ ማርኳል፡፡