የህወሓት ቡድን በሀሳብ ድርቀት የሚኖር ስብስብ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing የህወሓት ቡድን በሀሳብ ድርቀት የሚኖር ስብስብ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – የካቲት 24/2018 ዓ.ም.

የህወሓት ቡድን ወደ መሬት ሊወርድ በማይችል ኋላ ቀር ሀሳብ የሚመራ ቡድን በመሆኑ በለውጡ ማግስት በሀገር ደረጃ የመጣውን ለውጥ ባለመቀበሉ በሕዝቡ ብቻ ሳይሆን በራሱ ሕልውና ላይ አደጋ የሚጥል ውሳኔ ሲወስን መቆየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢዜአ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባካሔዱት ቆይታ እንደገለጹት፣ ቡዱኑ በጭፍን የሚወስዳቸው እርምጃዎች የጤናማ ፓርቲ ባሕሪ ባለመሆናቸው አዲስ ነገር ለማምጣትም ሆነ ወደ ለውጥ መንገድ የመግባት ፍላጎት እና ሀሳብ የለውም ብለዋል፡፡

ዓለማችን ባለፉት ሀያ እና ሰላሳ ዓመታት ብዙ ለውጦች አስተናግዳለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የህወሓት ቡድን በየጊዜው የሚመጣውን ለውጥ ሳይቀበል የ19ኛው ክ/ዘመን አስተሳሰብ ላይ ተቸንክሮ የኖረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዘመኑን በሚመጥንና ለሕዝባችን ዘላቂ ጥቅምና ሀገራዊ ብልጽግና በሚያመጣ ሀሳብ እንደመር ያለውን ኃይል እንደጠላት በመፈረጅ ሕዝባችንን ለከባድ ጉዳት ዳርጎታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡድኑ ከለውጡ ኃይል ጋር ከመሥራት ይልቅ ወደ ግጭት የማምራት አባዜ የተጠናወተዉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የህወሓት ቡድን በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍና ተደጋጋሚ የጦርነት ሰቆቃ የዘረዘሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ቡዱኑ በስልጣን በቆየባቸው ዓመታት የአዲስቷ ኢትዮጵያ ሕዝቦች በመጠራጠርና እርስ በእርስ በጎሪጥ እንድንተያይ ለማድረግ መሥራቱን ጠቅሰዋል፡፡

ይህ ቡድን ዛሬም ከቃታ አስተሳሰብ ያልወጣና ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ቁሞ የቀረ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።

በምሩፅ ተስፋይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review