የቦሌ ኮሪደር ልማት ለመዝናኛና ስፖርት ስፍራዎች ልዩ ትኩረት የሰጠ ነው

You are currently viewing የቦሌ ኮሪደር ልማት ለመዝናኛና ስፖርት ስፍራዎች ልዩ ትኩረት የሰጠ ነው

AMN- የካቲት 27/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ከኡራኤል – ቦሌ መድኃኔዓለም እስከ ቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል የተዘረጋው የኮሪደር ልማት፣ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ ዘመናዊ የመዝናኛና የስፖርት ስፍራዎችን የያዘ ነው ።

ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል በአካባቢው የነበረውን የመዝናኛ ቦታዎች እጥረት በከፍተኛ ደረጃ የሚቀርፍ መሆኑ ተገልጿል።

የኮሪደር ልማቱ ዋና ትኩረት የመንገድ ስራ ብቻ ሳይሆን፣ ነዋሪዎችና ህፃናት በነፃነት የሚንቀሳቀሱባቸውን ስፍራዎች መፍጠር ነው።

ቀደም ሲል ለህፃናት መጫወቻነት የሚያገለግሉ ቦታዎች ባልነበሩበት በዚህ የንግድ ቀጠና፣ አሁን ላይ ህፃናት በደህንነት የሚጫወቱባቸው ቦታዎች ተገንብተዋል።

ወጣቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች አካላዊ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችሉ ዘመናዊ የስፖርት ሜዳዎች እና ማዘውተሪያ ስፍራዎች የኮሪደር ልማቱ አካል ሆኖ ተካቷዋል።

ለመዝናኛ የእግር ጉዞ እና ለሳይክል ተብለው የተለዩ መንገዶች የተገነባለት ሲሆን ፣ አካባቢውን ለጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ተመራጭ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው ።

በቆሻሻና በአላስፈላጊ ግንባታዎች ተሸፍነው የነበሩ ቦታዎች ፀድተው ለአይን ማራኪ በሆኑ አረንጓዴ ስፍራዎች ተተክተዋል።

ቀደም ሲል ለዓይን ማራኪ ያልነበረው የአካባቢው የህንፃዎች ዛሬ ላይ በቂ ዕድሳት ተደርጎላቸው ዘመናዊና ሳቢ መልክ እንዲይዙ መደረጉም ተደርጓል ።

የመዝናኛ ስፍራዎቹ ነዋሪዎች እርስ በርሳቸው እንዲገናኙና ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ ዕድል ይፈጥራሉ። በከተማዋ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚበዛበት በዚህ መስመር፣ አረንጓዴ ስፍራዎቹ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች የአእምሮ እረፍት የሚሰጡ ናቸው።

በኮሪደር ልማቱ ዘመናዊ መልክ የያዘው ይህ አካባቢ ለአገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች ሳቢ መዳረሻ እንዲሆን ተደርጎ መሰራቱም ተገልጿል።

ይህ የኮሪደር ልማት የአዲስ አበባን “ሰው ተኮር” የከተማ ግንባታ ራዕይ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ፕሮጀክት ተደርጎ የሚወሰድ ነው ።

በቶለሳ መብራቴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review