AMN -መጋቢት 3/2018 ዓ.ም
ከተማ አቀፉ የፖሊስ ሰራዊት የስፖርት ውድድር
“ተልዕኮን በጀግንነት ስፖርትን በውጤት” በሚል መሪ ሃሳብ ለ2ኛ ጊዜ እንደሚከናወን ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በጋር በመሆን የተዘጋጀው ውድድር ከመጋቢት 5-19/2018 እንደሚካሄድ ተጠቅሷል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ህዝብ ግንኑነት ሃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንዳሉት የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ ሃላፊነት ወስዶ በአስተማማኝነት ሁኔታ እየሰራ ያለው ፖሊስ በስፖርቱም ረገድ ተተኪዎችን በማፍራት በኩል የማይተካ ሚና እንደሚወጣ አንስተዋል።
ስፖርትና ፖሊስ የማይነጣጠሉ ናቸው ያሉት ኮማንደሩ በአካል እና በአዕምሮ የዳበረ ሰራዊት እንዲኖርም መርሁን አጠናከረን እናስቀጥላለን ብለዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ሰፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉም የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ሲነሳ የፖሊስ ሰራዊት ተቋም ቅድሚያ ይወስዳል ሲሉ ተናግረዋል።
ውድደሩ በርካታ ተተኪዎች ይገኙበታል ያሉት ቢሮ ሃላፊው ለዚህም ባለፈው የተካሄደው 1ኛው ሃገር አቀፍ ውድድር ማሳያ ነው ብለዋል።
በዘንድሮ ውድድር ከ1300 በላይ ስፖርተኞች በእግርኳስ ፣ በቮሊቦል ፣ በአትሌቲክስ ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ ፣ በገመድ ጉተታ እንዲሁም በዳርት ስፖርቶች ይሳተፋሉ። ውድድሮቹም በአምስት የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎች ላይ እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
በዳዊት ተስፋዬ