AMN መጋቢት 5/2018 ዓ.ም
የፖሊስ ሰራዊት ከሰላም ጥበቃ ተልዕኮው ጎን ለጎን፣ የሀገርን ስም የሚያስጠሩና ሰንደቅ ዓላማን በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ የሚያደርጉ ዝነኛ ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ የማይተካ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት
ዛሬ ማለዳ 2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀምሯል ብለዋል፡፡
“ተልዕኮን በጀግንነት፣ ስፖርትን በውጤት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታድየም በድምቀት ተጀምሯል።
በስድስት የስፖርት አይነቶች የሚካሄደው ይህ ውድድር፣ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡
የፖሊስ ሰራዊት ከሰላም ጥበቃ ተልዕኮው ጎን ለጎን፣ የሀገርን ስም የሚያስጠሩና ሰንደቅ ዓላማን በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ የሚያደርጉ ዝነኛ ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ የማይተካ ሚና እያበረከተ ይገኛል፣ ይህ ተሳትፎ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡