ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMM – መጋቢት 7/2018 ዓ.ም

በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረው ቀውስ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነደጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸዉን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል።

የነዳጅ አከፋፋዮች፣ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ፣ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በሃላፊነት ስሜት እንድንጠቀም ለማሳሰብ እወዳለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review