AMN-መጋቢት 18/2018 ዓ.ም
በፖላንድ የታርኖው ከተማ ነዋሪና ስሙ ያልተጠቀሰ አንድ ግለሰብ ለዘጠኝ ዓመታት ያህል 139 ጊዜ የመንጃ ፈቃድ የንድፈ-ሀሳብ ፈተናን በጽናት በመፈተን በመጨረሻም ስኬታማ ሆኗል።
ግለሰቡ ለዚህ ዓላማው ብቻ ከ1 ሺህ 800 በላይ ወጪ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ተፈታኞች በመጀመሪያዎቹ ሙከራዎች ቢሳካላቸውም እሱ ግን ሳይሰለች ለዓመታት ተመላልሷል።
በፖላንድ ከዚህ በፊት 163 ጊዜ ተፈትኖ ያለፈ ሰው ቢኖርም የዚህኛው ግለሰብ ታሪክ ልዩ የሚያደርገው ለዘጠኝ ዓመታት ያሳየው የማይበገር ጽናትና ለዓላማው የነበረው ታማኝነት ነው።
በአሁኑ ወቅት የንድፈ-ሀሳብ ፈተናውን በድል ያጠናቀቀው ይህ ግለሰብ ወደ ቀጣዩ ተግባራዊ የመኪና መንዳት የተ ግባር ፈተና የተሸጋገረ ሲሆን፣ታሪኩም ተስፋ ካልቆረጡ የማይታለፍ ጋራ የለም የሚል ትልቅ የጽናት ትምህርት ለዓለም ያስተማረ ሆኖ አልፏል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቦታል።
እርሶስ ለአላማዎ ስንት ጊዜ ለመሞከር ዝግጁ ነዎት? የኤ ኤም ኤን ማህበራዊ ትስስር ገፅ ቤተሰብ በመቀላቀል ሀሳብ አስተያየቶን ያጋሩን።
በሚካኤል ህሩይ