AMN – ሰኔ 19/2018 ዓ.ም
በምድብ ስድሰት የሚገኙት ስዊድን እና ጃፓን 1ለ1 በመለያየት ተያይዘው ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።
ዴይዘን ሜኤዳ ለጃፓን አንቶኒ ኢላንጋ ደግሞ ለስዊድን ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ጃፓን አምስት ፣ ስዊድን ደግሞ አራት ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ይዘው ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።
ምድቡን በበላይነት ያጠናቀቀችው ኔዘርላንድስ ቱኒዚያን 3ለ1 አሸንፋለች።

ብሪያን ብሮቢ ፣ ፖል ቫን ሄከ እና ኤልያስ ሽሂሪ በራሱ ላይ ያስቆጠሯቸው ግቦች ኔዘርላንድስን አሸናፊ አድርገዋል።
የሮናልድ ኩመን ቡድን ሰባት ነጥብ በመያዝ ምድቡን በበላይነት ስታጠናቅቅ ፣ ቱኒዚያ ሦስቱንም ጨዋታዎች ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።