ቢሮው የንግድ ግብይቶችን በደረሰኝ በመፈፀም የላቀ የህግ ተገዢነት ደረጃ ላስመዘገቡ ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ሰጠ፡፡

You are currently viewing ቢሮው የንግድ ግብይቶችን በደረሰኝ በመፈፀም የላቀ የህግ ተገዢነት ደረጃ ላስመዘገቡ ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ሰጠ፡፡

AMN-ሰኔ/ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በደረሰኝ በመግዛትና በመሸጥ፣ በግብር አከፋፈል፣ በህግ ተገዢነት ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ 3 ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ሰጥቷል።

በመዲናዋ ትልቁ የገበያ ስፍራ በሆነው በመርካቶ በተዘጋጀ የእውቅና መርሀ ግብር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አቡድልቃድር ሬድዋን ቢሮው የታክስ ህግን አክብረው የሚሰሩ ግብር ከፋዮች ለሌሎች አርአያነት ባለው መልኩ እውቅና መስጠቱ የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡

ሁሉም ግብር ከፋይ ጤነኛ የደረሰኝ አጠቃቀም ባህል በማዳበር የህግ ተገዢነት ደረጃውን ለማላቅ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ መደገፍ ይጠበቅበታልም ነው ያሉት ኃላፊው፡፡

በአሁነ ወቅት በከተማዋ ሁለንተናዊ ልማት የግብር ከፋዮች ሚና የላቀ መሆኑን በመግለፅ ይህ እንዲጠናከር ህገወጦች ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገቡ ከመቅጣት ባሻገር በህጋዊ መንገድ የሚሰሩትን ደግሞ ማበረታታት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በበኩላቸው ቢሮው በከተማዋ ክብርት ከንቲባ በተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት ከግብር ከፋዮች ጋር ተቀራርቦና ተጋግዞ ለመስራት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የዕለቱ በደረሰኝ ግብይት የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና ፕሮግራምም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑንም መናገራቸውን ቢሮው ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል በላከው መረጃ ገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review