2ኛው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርት ውድድር ዛሬ ይጠናቀቃል

You are currently viewing 2ኛው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርት ውድድር ዛሬ ይጠናቀቃል

AMN – መጋቢት 19 2018 ዓ.ም

ከመጋቢት 6 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታድየም በሚከናወኑ መርሃ ግብሮች ፍፃሜውን ያገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በጋራ የተዘጋጀው ይህ ታላቅ ስፖርታዊ መድረክ፤ “ተልዕኮን በጀግንነት፣ ስፖርትን በውጤት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ ቆይቷል።

በውድድሩ ማጠቃለያ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የፖሊስ አዛዦችና አባላት እንድ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ ይጠበቃል።

ውድድሩ የፖሊስ አባላትን ዝግጁነት ከማሳደግ ባለፈ በስፖርታዊ ጨዋነትና በውጤታማነት ረገድ መልካም ተሞክሮዎች የታዩበት እንደነበር ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review