AMN – መጋቢት 20/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የተሰሩት የመንገድ ዳር መብራትና የደህንነት ካሜራዎች በከተማዋ ይፈፀሙ የነበሩ ወንጀሎች ለመቀነስ እንዳስቻሉ የውስጥ ለውስጥና የመንገድ መብራት ማስበራት ግብረሃይል አስተወቀ።
ግብረ ሀይሉ በልደታ ክፍለ ከተማ በሶስት ወረዳዎች የተሰሩ የመንገድ ዳር መብራትና የደህንነት ካሜራዎችን ጨምሮ ለወንጀል ቅነሳ የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝቷል።
በመርሃ ግብሩ የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢና የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ አዲስ አበባ ሰላሟ የተረጋገጠ ሆና እንድትቀጥል እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የመንገድ ዳር መብራትና የደህንነት ካሜራዎችን ጨምሮ በተሰሩ ስራዎች በከተማዋ ይፈፀሙ የነበሩ ወንጀሎች ስለመቀነሳቸውም ተናግረዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ልዕልቲ ግደይ ፣ በከተማዋ የተሰራው የኮሪደር ልማት ወንጀልን በአከላከል ረገድ የማይተካ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።
በክፍለ ከተማው ወንጀልን ለመከላከል የተሰራው ስራ ውጤታማ ቢሆንም በቀጣይ የጎደሉትን ለመሙላት በትጋት እንደሚሰራ ገልፀዋል።
በፅዮን ማሞ