ለሕጻናት አእምሯዊና አካላዊ እድገት ቅድሚያ ሰጥታ የምትሰራዉ የአፍሪካ መዲና-አዲስ አበባ

You are currently viewing ለሕጻናት አእምሯዊና አካላዊ እድገት ቅድሚያ ሰጥታ የምትሰራዉ የአፍሪካ መዲና-አዲስ አበባ

AMN- ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ በመልካም ተሞክሮነት ስሟን ካስጠሩ በርካታ ተግባራት አንዱ ለሕጻናት የምትመች መዲና እየሆነች መምጣቷ ነው፡፡

የከተማ መስተዳደሩ አዲስ አበባ ህጻናትን ለማሳደግ የምትመች ምርጧ የአፍሪካ ከተማ ለማድረግ የሰነቀውን ራዕይ ለማሳካት የወጠነው የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ስኬታማ አፈጻጸም እያሳየ ይገኛል።

መስተዳድሩ 1.3 ሚሊዮን ገደማ ህጻናት በተለይ ደግሞ 330 ሺህ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ህጻናት ጋር ለመድረስ የሚያስችል ልዩ መርሃ ግብር ቀርጾ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ኘሮግራሙ ከተጀመረበት ከ2ዐ15 ጀምሮ እስከ በጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ድረስ ከ5 ሺህ በላይ የህፃናት መጫዎቻዎችና ከ1ሺህ በላይ የህፃናት ማቆያዎች ገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ ሲሆን በካዘንቺስ 5 ሔክታር መሬት ላይ የህፃናት ዓለም እየተገነባ መሆኑ የከተማ አስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እናቶች እና ህጻናት የአልሚ ምግብ ድጋፍ በማረግ ላይ ከመሆኑም ባሻገር በጤና ጣቢያዎች ለህጻናት የእድገት ሁኔታ ክትትል ያደርጋል፡፡

በክትትሉ የእድገት ውስንነት የታየባቸው ሁሉም ህጻናት ተገቢውን የህክምና ክትትል ያገኛሉ ፣ አካላዊ እድገት ውስንነት ለታየባቸው ህጻናትም ችግራቸውን ታሳቢ ያደረግ የዊልቼር ድጋፍ ይደረጋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለህጻናት ቅድሚያ ሰጥቶ በሚያከናዉናቸዉ ተግባራት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ብቻ በከተማው የነበረው የህጻናት የዕድገት ሁኔታ በ2.7% ተሻሽሏል፡፡

ወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review