የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር እያረጋገጠ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር እያረጋገጠ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN- ሚያዝያ 7/2018 ዓ.ም

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር ስር እየሰደደ መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልፀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፣ በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ አሎማ ክላስተር በበጋ መስኖ የለማውን የደረሰ የስንዴ ማሳ መመልከታቸውን ገልጸዋል።

የመደመር መንግሥት ለበጋ መስኖና ለስንዴ ምርታማነት የሰጠው ትኩረት የዜጎችን ሕይወት እየቀየረና የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት እያረጋገጠ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ዛሬ የተመለከትነው የስንዴ ልማትም የራዕያችንን ውጤት፣ የሀሳባችን መሬት መንካትና ፍሬ የማግኘታችን ተጨባጭ ማሳያ ነው ሲሉም አክለዋል።

አርሶ አደሩን በተደመረ አቅም በማትጋት የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን በመጠቀም በሁሉም መስክ ሀገርን የማሻገር ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወሎ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ፣ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸው እና አርሂቡ ብለው ለተቀበሏቸው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለወሎ ሕዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

እንደ ቦርከና ወንዝ የማይነጥፈው ገራገርነታችሁ፣ የማይጠገብ ትኅትናችሁ፣ እንደ ጦሳ ተራራ የገዘፈው መስተንግዶና ደማቅ አቀባበላችሁ ልባችንን በሐሴት ሞልቶታል በማለትም ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review