ኮፕ32ን ለማስተናገድ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ የእስካሁን ሥራዎችን ገመገመ

You are currently viewing ኮፕ32ን ለማስተናገድ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ የእስካሁን ሥራዎችን ገመገመ

AMN – ሚያዝያ 9/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የኮፕ32 ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማሰናዳት ‎የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መካሄዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ኮሚቴ በይፋ በማቋቋም ዝግጅቷን ቀደም ብላ መጀመሯን ገልጸዋል።

ይህን ሂደት በግልጽ ግብ እና በላቀ ምልከታ ለመምራት ቁልፍ አመራር መመደባቸውንና ይህን ተከትሎ የኮፕ ፕሬዝደንት መዋቅር የተቀናጀና የላቀ ውጤት የሚያስገኙ የቅድሚያ ተግባራቱን መጀመሩን ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ፣ ዛሬ ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በነበረን ስብሰባ፤ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ የእስካሁን ሥራዎችን በመገምገም ክፍተቶችን የመለየት እና ሁሉም ጥረቶቻችን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተዳሷል ብለዋል።

በመድረኩ ከግምገማ ባሻገር የጋራ ቀጣይ አቅጣጫ መቀመጡንም ነው የገለጹት።

ትኩረታችን ግልጽ ነው፤ በጠንካራ ትብብር፣ በተዋሃደ ታላቅ ርዕይ እና የጋራ ጽኑ ትጋት ተናበን ይህን ዓለም አቀፍ ሁነት በልህቀት በማስተናገድ የሀገርን ታላቅነት ዳግም ማሳየት ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review