AMN ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ አምስት ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት:-
በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ያቀርባሉ፦
ማዕከላቱ ምርቶች በቀጥታ ከአምራች ገበሬዎች ስለሚያመጡ፣ ከመደበኛው ገበያ ከ15% እስከ 20% የሚደርስ የዋጋ ቅናሽ ያቀርባሉ።
የደላላ ጣልቃ ገብነት አስቀርተዋል፦
በገበሬውና በተጠቃሚው መካከል የሚገቡና ያላግባብ ዋጋ የሚጨምሩ ህገ-ወጥ ደላሎችን በማስቀረት ምርቱ በትክክለኛ ዋጋ ለህዝብ እንዲደርስ አስችሏል።
ትኩስና ጥራት ያለው ምርት ያቀርባሉ፦
የግብርና ምርቶች (በተለይም አትክልትና ፍራፍሬ) ሳይቆዩና ሳይበላሹ በቀጥታ ከእርሻ ቦታው ስለሚመጡ ህብረተሰቡ የተሻለ ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያገኝ አድርጓል።
ፍትሃዊ የንግድ ስርዓትን ያሰፍናሉ፦
ማዕከላቱ ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ስላላቸው፣ ነዋሪው ምርቶችን በሚገዛበት ወቅት በትክክለኛ ሚዛንና ግልጽ በሆነ የዋጋ ተመን እንዲያገኝ አስችሏል።

የገበያ ተደራሽነት ያሳድጋሉ፦
ማዕከላቱ በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች (ላፍቶ፣ አቃቂ፣ ኮልፌ፣ ለሚ ኩራ) መገንባታቸው ነዋሪዎች ምርቶችን ለማግኘት ረጅም ርቀት ሳይጓዙ በቅርብ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
የአቅርቦት መረጋጋት ይፈጥራሉ፦
በ246 የቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች ጭምር በቂ ምርት እንዲቀርብ በማድረጋቸው፣ በተለይም በበዓላትና በሳምንቱ መጨረሻ የሚታየውን የምርት እጥረትና የዋጋ መናር እየተከላከሉ ነው።
ዘመናዊና ምቹ አካባቢ ይፈጥራሉ፦
ማዕከላቱ ዘመናዊ በመሆናቸው እንደ ድሮው ጭቃና ግፊያ ሳይኖርባቸው ህብረተሰቡ በንጹህና በሰለጠነ አካባቢ ግብይቱን እንዲፈጽም ያስችላሉ።

ዘላቂነት ያለው የምግብ አቅርቦት፦
በከተማዋ ውስጥ የምርት አቅርቦት እንዳይቆረጥ በማድረግ በኩል ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
የከተማዋን ገጽታ መለወጥ፦
ያረጁና ጽዳታቸው ያልተጠበቀ የገበያ ቦታዎችን በዘመናዊና ንጹህ የግንባታ ውጤቶች መተካታቸው ለአዲስ አበባ የሥልጣኔ ገጽታ ተጨማሪ ውበት ሆኗል። – የከንቲባ ጽ/ቤት