ለዘመናዊ የቅርስ ጥበቃ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing ለዘመናዊ የቅርስ ጥበቃ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

AMN- ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም

ለዘመናዊ የቅርስ ጥበቃ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባልስልጣኑ የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን በሚል 3ኛውን የምርምር ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚህ ሀገራዊ ጉባኤ ላይ 13 ያክል ጥናቶች የሚቀርቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል ቅርስና ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚል ጥናት ይገኝበታል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በዚህ የጥናት ጉባኤ የሚቀርቡ የምርምር ውጤቶች በቅርስ ጥበቃ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመለየት የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂ የቅርስ ጥበቃ በማድረግ ዘርፉን ለኢኮኖሚ እድገት ለመጠቀም እየሰራች ትገኛለች።

ቀደምት ታሪክና ቅርስ ያላት ሀገር ኢትዮጵያ ቅርሶችን በዘመናዊ ሂደት ለዓለም ማስተዋወቅ ይጠበቅባታል።

በዚህ ዘርፍ የሚደርጉ ምርምሮችም ለስራችን አጋዥ ናቸው ብለዋል።

ጉባኤው ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑም ታውቋል።

በረውዳ ሸምሱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review