ከ50 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል

You are currently viewing ከ50 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል

AMN ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም

‎ከ50 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሚሊዮን 500 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ የመራጮችን ምዝገባ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ በ48 ሺህ 829 የምርጫ ጣቢያዎች ፣ በምርጫ ቦርድ ድረ-ገፅና በምርጫዬ መተግበሪያ በተከናወነ የመራጮች ምዝገባ ከ50 ሚሊዮን 500 ሺህ በላይ ዜጎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

ከተመዝጋቢዎቹ ውስጥ ከ45 ሚሊዮን የሚበልጡት በምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ ሲሆኑ ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ በዲጂታል መመዝገባቸውን ሰብሳቢዋ አብራርተዋል።

የካቲት 28 ቀን የተጀመረው የመራጮች ምዝገባ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ቢጠናቀቅም ተጠቃለው ለቦርዱ ያልደረሱ መረጃዎች እንዳሉ ተመላክቷል።

በካሳሁን አንዱአለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review