እውነተኛ እውቀት ችግሮችን ደጋግሞ ማውራት ሳይሆን ለችግሮች መፍትሄ ማፍለቅና ችግርን ወደ ድል መቀየር ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing እውነተኛ እውቀት ችግሮችን ደጋግሞ ማውራት ሳይሆን ለችግሮች መፍትሄ ማፍለቅና ችግርን ወደ ድል መቀየር ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ሚያዝያ 16/2018 .

“በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ በይፋ ተጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አውደ ርዕዩን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ እውነተኛ እውቀት ችግሮችን ደጋግሞ ማውራት ሳይሆን ለችግሮች መፍትሄ ማፍለቅና ችግርን ወደ ድል መቀየር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የአውደ ርዕዩ ዋና ዓላማ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ የቀሰሙትን የንድፈ ሀሳብ እውቀት በተግባር እንዲያሳዩና የውስጥ ተሰጥኦዋቸውን በነጻነት እንዲገልጹ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው።

ከዚህም ባለፈ አውደ ርዕዩ ተማሪዎች ለሰሯቸው የፈጠራ ስራዎች የሚበረታቱበትና በትብብር የመስራት ልምዳቸውን እርስ በእርስ የሚለዋወጡበትን ሰፊ እድል ይዞ መቅረቡን ገልፀዋል።

አዲስ አበባን የሳይንስና ፈጠራ ማዕከል ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ በአሁኑ ወቅት ውጤቱ በተጨባጭ መታየት መጀመሩን ገልጸው፤ ይህ ውጤታማ ጅምሮ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በአውደ ርዕዩ ላይ የፈጠራ ስራቸውን ላቀረቡ ተማሪዎችና መምህራንም ከንቲባዋ አበረታች መልዕክት አስተላልፈዋል።

የቀረቡት የፈጠራ ስራዎች ወደፊት አድገውና በልጽገው ለከተማዋ፣ ለሀገር አልፎም ለዓለም የሚተርፍ በረከት ሊሆኑ እንደሚችሉ አስተዳደሩ ትልቅ ተስፋ ማድረጉን ጠቁመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review