ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ

AMN- ሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም

ማንችስተር ዩናይትድ በ34ኛ ሳምንት መርሐግብሩ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚያሳትፈው ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ ብሬንትፎርድን ይገጥማል።

ዩናይትድ የዛሬውን ጨምሮ ከቀሩት አምስት ጨዋታዎች ሁለቱን ማሸነፍ ያሰበውን እንዲያሳካ ያደርገዋል። የዛሬ ተጋጣሚ ብሬንትፎርድ ግን በቀላሉ እጅ የሚሰጥ አይደለም።

ዋና አሰልጣኙ እና ወሳኝ ተጫዋቾቹን በማጣቱ በርካቶች እንዳይወርድ የሰጉለት ብሬንትፎርድ አስገራሚ የውድድር ዓመት እያሳለፈ ይገኛል። በመጀመሪያው ዙርም ዩናይትድ 3ለ1 ማሸነፉ ይታወሳል።

በዛሬ ጨዋታ በዩናይትድ በኩል ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በቅጣት አይገባም። እንግሊዛዊው ተከላካይ ሀሪ ማጓየር ግን ቅጣቱን ጨርሶ ወደ ሜዳ ይመለሳል። ከመጠነኛ ጉዳቱ ያገገመው ሌኒ ዮሮ ግን መግባቱ አልተረጋገጠም።

በዛሬው ጨዋታ በዩናይትድ በኩል ለቡድን አጋሮቹ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ታሪክ ለመስራት የተቃረበው ቡርኖ ፈርናንዴዝ እንዲሁም በብሬንትፎርድ በኩል 21 የሊግ ግቦች ያሉት ኢጎር ቲያጎ ይጠበቃሉ።

በክረምት የተጫዋቾች ዝውውር ብሬንትፎርድን ለቆ ማንችስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ብሪያን ምቡሞ የቀድሞ ክለቡን ለመግጠም ይዘጋጃል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ዩናይትድ በ58 ነጥብ ሦስተኛ ላይ ሲገኝ ፣ ብሬንትፎርድ በ48 ነጥብ ዘጠነኛ ላይ ተቀምጧል።

ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ባደረጓቸው አምስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ሁለት ሁለት ድል አስመዝግበው በአንዱ ነጥብ ተጋርተዋል።

በኦልድትራፎርድ የሚከናወነው የዛሬ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይጀምራል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review