በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የነበረው ዓለም አቀፍ የሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ ተጠናቀቀ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የነበረው ዓለም አቀፍ የሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ ተጠናቀቀ

AMN-ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም

በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የነበረው ዓለም አቀፍ የሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ (City Mountain Bike Eliminator Pro League) ተጠናቋል።

ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በታላቅ ድምቀት በተከናወነው ዓለም አቀፍ የሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ ላይ ለተሳተፉ ተወዳዳሪዎች ፣አመራሮች እና ልዑካናቸው በውቧ አራዳ ፓርክ በነፋሻማ አየር የታጀበ ልዩ የእራት ፕሮግራም በማዘጋጀት የአዲስ አበባ ቆይታቸውን ይበልጥ አስደሳች እና ልዩ አድርገንላቸዋል።

በውድድሩ ላይ የተሳተፉ ተወዳዳሪዎች በሰጡት አስተያየት ፣ውድድሩ የተካሄደበት ስፍራና የአዲስ አበባ ከተማ ገፅታ እጅግ አስደሳች እንደነበር ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ይህን መሰል ትልቅ ዓለም አቀፍ ውድድር በአህጉሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በብቃትና በከፍተኛ ጥራት ማዘጋጀቷም ለስፖርት ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ማሳያ መሆኑን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review