AMN -ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለሀገራቸው እና ለሕዝባቸው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ጊዜንና ትውልድን የሚሻገር መሆን እንደሚገባው የዘርፉ ምሁራን አጽንኦት ይሰጣሉ፡፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የሀገራቸውን ማንነት በማጉላት፣ የሕዝብን አእምሮ በመገንባት እና አብሮነትን በማጠናከር የላቀ ድርሻ ላበረከቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በታሪካዊ አደባባዮችና ቦታዎች የመታሰቢያ ሐውልት በማቆም ክብር ሰጥቷል።

እነዚህ ባለሙያዎች የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ ከባህላዊ ቅኝቶች ጋር በማቀናጀት ለዓለም አቀፍ መድረክ ያበቁ፣ በድምፃቸው ጥንካሬና ልዩ ስሜት አድማጭን ማማለል የቻሉ ድንቅ ባለሙያዎች ናቸው።
በሙዚቃዎቻቸው አማካኝነት የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሀገር ፍቅር እና የሰላም መልእክቶችን በማስተላለፍ የሕዝብን ስሜት ገልጸዋል። ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና አቅመ-ደካሞች ድጋፍ በሚያደርጉ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ በንቃት በመሳተፍ የብዙዎችን ሕይወት ታድገዋል።

የሀገር ውስጥ ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅና የቅርብ ጊዜ ትውልድም ባህሉን እንዳይረሳ አድርገዋል። የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍና ተውኔት በማበልጸግ፣ በቋንቋ ቅርስ ጥናት እና በኪነ ጥበብ ፈጠራዎች እጅግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የዘመናችን ባለውለታዎች ናቸው።

በርካታ ተውኔቶችን፣ ግጥሞችን እና መጽሐፍትን በማዘጋጀት የሀገሪቱን ሥነ ጽሑፍ ከፍ እንዲል አድርገዋል። ማራኪ የኪነ ጥበብ ሥራዎቻቸው የሀገርን ሉዓላዊነትና የሕዝብን አንድነት በማጉላት ለትውልድ ታሪካዊ ቅርስ ሆነው አገልግለዋል።
የዓለም አቀፍ ታላላቅ ደራሲያን ሥራዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ቋንቋ በመተርጎም የሀገሪቱን ሥነ ጽሑፍ ከዓለም ጋር ያገናኙ ባለውለታዎችም ናቸው።

የብሔር ብሔረሰቦችን ባህል፣ ሙዚቃ እና ሥነ-ጽሑፍ በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ፣ የአብሮነት እና የሰላም ምልክት የሆኑ ባለሙያዎች ናቸው።
የተለያዩ ማኅበረሰቦችን መቻቻል እና አንድነት በሥራዎቻቸው አጉልተው በማሳየት የመቻቻልና የአንድነት ምልክት የሆኑና ለሀገር ሰላም ታላቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የአካባቢውን ባህል፣ ታሪክ እና ሥነ-ጽሑፍ በስራዎቻቸው በሰፊው በማስተዋወቅ የሀገር ሀብት እንዲሆን አድርገዋል።

እነዚህ የኪነ ጥበብ ሰዎች የሰሯቸው ሥራዎች ለጊዜው ብቻ ሳይሆን የሀገርን ማንነት ለትውልድ በማስተላለፍ፣ የሕዝብን አእምሮ በመገንባት እና አብሮነትን በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ ማበርከታቸውን የተለያዩ የህትመትና የድምጽ ቅጂ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በአስማረ መኮንን