በአዲስ አበባ የተመለከትናቸው ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ ተምሳሌት የሚሆኑ ናቸው

You are currently viewing በአዲስ አበባ የተመለከትናቸው ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ ተምሳሌት የሚሆኑ ናቸው

AMN ሚያዝያ 29/2018

በአዲስ አበባ የተመለከትናቸው ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ ተምሳሌት መሆናቸውን የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡

የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።

በጉባኤው ለመታደም ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 321 ሚሊየን በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ያሏቸው 61 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ ከትመዋል።

በተጨማሪም 150 ሚሊየን ተከታዮች ያላቸው 120 ኢትዮጵያውያን የይዘት ፈጣሪዎች በጋራ በመሰባሰብ፣ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ አዲስ የዲጂታል ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል፡፡

ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ጉባዔ “ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ” የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ የተገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶችንና የኮሪደር ልማቶችን እንዲሁም ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ኬንያዊው የጉብኝቱ ተሳታፊ በቴ ጆጉ በሰጠው አስተያየት፤ በአዲስ አበባ የተመለከታቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶችና የኮሪደር ልማቶች ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባለፈ ገጽታዋን በእጅጉ መቀየራቸውን ገልጿል።

የአዲስ አበባ የከተማ እድገት፣ የጎዳናዎች ስፋትና ውበት የሚያስደንቅ መሆኑን በአካል ማረጋገጡንም ተናግሯል።

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተመከተው የቴክኖሎጂ ትኩረትም ሀገሪቱ ለዘመናዊ አሰራር የሰጠችውን ግምት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሷል።

በከተማዋ የታዩት ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ ተምሳሌት እንደሚሆኑም ገልጿል።

ከቡርኪናፋሶ የመጣው ማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ጃጓር ኢኮ እንዳለው፤ አዲስ አበባን በአካል በመጎብኘቱ መደሰቱን ገልጾ፣ ከተማዋ ሁሉም አፍሪካዊ ሊማርባት የሚገባ የልማት ማዕከል መሆኗን መመልከቱን መናገሩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባይነት መደሰቱን የገለጸው የማህበራዊ ሚዲያ አንቂው፣ ወደ ሀገሩ ሲመለስም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆኖ እንደሚሰራ አረጋግጧል።

የአዲስ አበባ ፈጣን እድገት ለአህጉሪቱ ትልቅ ተሞክሮ መሆኑንም ጨምሮ ጠቅሷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review