የአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

You are currently viewing የአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

AMN – ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች፣ በዛሬው ዕለት በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ተሳታፊዎቹ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩትንና የጉለሌ እንጀራ ፋብሪካን የጎበኙ ሲሆን፣ በወቅቱም በተመለከቷቸው የቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች ላይ ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት ገልጸዋል።

ተጽዕኖ ፈጣሪዎቹ በምልከታቸው ወቅት እንደገለጹት፤ አፍሪካ የራሷ የሆነ ሀገር በቀል ዕውቀትና እምቅ የወጣት ኃይል ያላት አህጉር በመሆኗ ይህንን አቅም በአግባቡ መጠቀም የሁሉም የጋራ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል።

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እየታየ ያለው ተጨባጭ ለውጥም ለአህጉሪቱ ዕድገት እንደ ትልቅ ማሳያ ሊወሰድ እንደሚችል አመልክተዋል።

ይህ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ጉባኤ ዋነኛ ዓላማው በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር፣ በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ድምፅ ማሰማት የሚችሉበትን ዕድል ማመቻቸት ነው።

በተጨማሪም አፍሪካ ያላትን ትክክለኛና ውብ ገጽታ በማጉላት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማስተዋወቅ ስራ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራም ተገልጿል።

በአጠቃላይ አፍሪካ በማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ልጆቿ አማካኝነት ያላትን እምቅ ሀብትና ተስፋ ሰጪ ለውጦች ለዓለም በማጋራት፣ የአህጉሪቱን ገጽታ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጉባኤው ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

በዮናስ አስረስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review